16 በምድረ በዳ ፍትሕ ይሰፍናል፤በለሙም መሬት ጽድቅ ይኖራል፤
17 የጽድቅ ፍሬ ሰላም፣የጽድቅ ውጤትም ጸጥታና ለዘላለም መታመን ይሆናል።
18 ሕዝቤ ሰላማዊ በሆነ መኖሪያ፣በሚያስተማምን ቤት፣ጸጥ ባለም ስፍራ ዐርፎ ይኖራል።
19 ደኑ በበረዶ ቢመታ፣ከተማውም ፈጽሞ ቢወድም፣
20 በየወንዙ ዳር ዘር የምትዘሩ፣በሬዎቻችሁንና አህዮቻችሁን በነጻነት የምታሰማሩ፣ምንኛ የተባረካችሁ ናችሁ።