1 “ላልለመኑኝ ራሴን ገለጥሁላቸው፤ላልፈለጉኝ ተገኘሁላቸው።ስሜን ላልጠራ ሕዝብ፣‘አለሁልህ፤ አለሁልህ’ አልሁት።
2 ለዐመፀኛ ሕዝብ፣መልካም ባልሆኑ መንገዶች ለሚሄዱ፣የልባቸውን ምኞት ለሚከተሉ፣ቀኑን ሙሉ እጆቼን ዘረጋሁ።ዘወትር በፊቴ የሚያስቈጡኝ ሕዝቦች፣
3 በአትክልት ቦታዎች መሥዋዕት የሚያቀርቡ፣በሸክላ መሠዊያዎች ላይ ዕጣን የሚያጥኑ፣ዘወትር በፊቴ የሚያስቈጡኝ ሕዝብ ናቸው፤
4 በመቃብር መካከል የሚቀመጡ፣በስውር ቦታዎች የሚያድሩ፣የዕሪያ ሥጋ የሚበሉ፣ማሰሮዎቻቸውን በረከሰ ሥጋ መረቅ የሚሞሉ ናቸው፤
5 ‘ዘወር በል፤ አትቅረበኝ፤አትጠጋኝ፤ እኔ ከአንተ ይልቅ ቅዱስ ነኝ’ የሚሉ ናቸው።እንዲህ ያለው ሕዝብ በአፍንጫዬ ዘንድ እንደ ጢስ፣ቀኑን ሙሉ እንደሚነድድ እሳት ነው።