23 “ሳኦልና ዮናታን በሕይወት እያሉ፣የሚዋደዱና የሚስማሙ ነበሩ፤ሲሞቱም አልተለያዩም፤ከንስርም ይልቅ ፈጣኖች፣ከአንበሳም ይልቅ ብርቱዎች ነበሩ።
24 “እናንት የእስራኤል ቈነጃጅት ሆይ፤ሐምራዊ ቀሚስና ቀጭን ፈትል ላለበሳችሁ፣ልብሶቻችሁንም በወርቀ ዘቦ ላስጌጠላችሁ፣ለሳኦል አልቅሱለት።
25 “ኀያላን እንዴት እንዲህ በጦርነት ወደቁ!ዮናታን በኰረብቶችህ ላይ ተወግቶ ሞቶአል።
26 ወንድሜ ዮናታን ሆይ፤ እኔ ስለ አንተ አዘንሁ፤አንተ ለእኔ እጅግ ውድ ነበርህ፤ፍቅርህ ለእኔ ድንቅ ነበረ፤ከሴት ፍቅርም ይልቅ ግሩም ነበር።
27 “ኀያላኑ እንዴት ወደቁ!የጦር መሣሪያዎቹስ እንዴት ከንቱ ይሁኑ!”