2 ሳሙኤል 3:29-35 NASV

29 ደሙ በኢዮአብ ራስና በአባቱ ቤት ሁሉ ላይ ይሁን፤ ፈሳሽ ነገር የሚወጣው ወይም አሠቃቂ የቈዳ በሽታ ያለበት፣ በምርኵዝ የሚሄድ አንካሳ፣ ወይም በሰይፍ ተመቶ የሚወድቅ ወይም የሚበላው ያጣራብተኛ ከኢዮአብ ቤት አይታጣ።”

30 አበኔር ገባዖን ላይ በተደረገው ጦርነት የኢዮአብንና የአቢሳን ወንድም አሣሄልን ገድሎት ስለ ነበር፣ እነርሱም አበኔርን ገደሉት።

31 ከዚያም ዳዊት ለኢዮአብና አብሮት ለነበረው ሕዝብ ሁሉ፣ “ልብሳችሁን ቀዳችሁ፣ ማቅ ለብሳችሁ በአበኔር ፊት አልቅሱ” አላቸው፤ ራሱ ንጉሥ ዳዊትም አስከሬኑን አጀበ።

32 ከዚያም አበኔርን በኬብሮን ቀበሩት፤ ንጉሡም በአበኔር መቃብር ላይ ጮኾ አለቀሰ፤ ሕዝቡም ሁሉ እንደዚሁ አለቀሱ።

33 ንጉሡም ለአበኔር ይህን የሐዘን እንጒርጒሮ ተቀኘ፤“አበኔር እንደ ተራ ሰው ይሙት?

34 እጆችህ አልታሰሩም፤እግሮችህ በእግር ብረት አልገቡም፤ሰው በክፉ ሰዎች ፊት እንደሚወድቅአንተም እንደዚሁ ወደቅህ።”ሕዝቡም ሁሉ እንደ ገና አለቀሱለት።

35 ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ እህል በሚቀምስበት ሰዓት ወደ ዳዊት መጥተው ምግብ እንዲበላ አጥብቀው ለመኑት። ዳዊት ግን፣ “ፀሓይ ከመጥለቋ በፊት እንጀራ ወይም ሌላ ነገር ብቀምስ፣ እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ፤ ከዚህም የባሰ ያምጣብኝ” ብሎ ማለ።