መሳፍንት 5:25-31 NASV

25 ውሃ ለመነ፤ ወተት ሰጠችው፤ለመኳንንት በሚገባ ዕቃ፣ እርጎ አቀረበችለት።

26 እጇዋ ካስማ ያዘ፤ቀኝ እጇም የሠራተኛ መዶሻ ጨበጠ፤ሲሣራን መታችው፤ ራሱንም ተረከከችው፤ክፉኛ ወጋችው፤ ጆሮ ግንዱን በሳችው።

27 በእግሯ ሥር ተደፋ፤ ወደቀ፤በዚያም ተዘረረ፤ በእግሯ ሥር ተደፋ፤ወደቀ፤ በተደፋበት በዚያ ወደቀ፤ሞተም።

28 “የሲሣራ እናት በመስኮት ተመለከተች፤በዐይነ ርግቡ ቀዳዳም ጮኻ ተጣራች፤‘ለምን ሠረገላው ሳይመጣ ዘገየ?የሠረገሎቹስ ድምፅ ለምን ጠፋ?’ አለች።

29 ብልሃተኞች ወይዛዝርቷም መለሱላት፤እርሷ ግን ለራሷ እንዲህ አለች፤

30 ‘ምርኮ አግኝተው እየተከፋፈሉ፣እያንዳንዱም ሰው አንዲት ወይም ሁለት ልጃገረዶች እየወሰደ አይደለምን?ይህ ሁሉ ምርኮ፣ በቀለም ያጌጡ ልብሶችለሲሣራ ደርሰውት፣በጌጣጌጥ የተጠለፉ ልብሶች ለአንገቴይዞልኝ እየመጣ አይደለምን?’

31 “እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶችህ ሁሉ ይጥፉ፤አንተን የሚወዱህ ግን፣ የንጋት ፀሐይበኀይል እንደሚወጣ እንዲያ ይሁኑ።”ከዚያም በኋላ ምድሪቱ ለአርባ ዓመት ሰላም አገኘች።