12 በፊቴ ለመቅረብ ስትመጡ፣ይህን ሁሉ እንድታመጡ፣የመቅደሴን ደጅ እንድትረግጡ ማን ጠየቃችሁ?
13 ከንቱውን መባ አታቅርቡ፤ዕጣናችሁን እጸየፋለሁ፤የወር መባቻ በዓላችሁን፣ሰንበቶቻችሁን፣ ጉባኤያችሁንናበክፋት የተሞላውን ስብሰባችሁን መታገሥአልቻልሁም።
14 የወር መባቻችሁንና የተደነገጉ በዓሎቻችሁንነፍሴ ጠልታለች፤ሸክም ሆነውብኛል፤መታገሥም አልቻልሁም።
15 እጆቻቸሁን ለጸሎት ወደ እኔ ስትዘረጉ፣ዐይኖቼን ከእናንተ እሰውራለሁ፤አብዝታችሁ ብትጸልዩም እንኳ አልሰማችሁም፤እጆቻችሁ በደም ተበክለዋል፤
16 ታጠቡ፤ ራሳችሁንም አንጹ፤ክፉ ሥራችሁን ከፊቴ አርቁ፤ክፉ ማድረጋችሁን ተዉ፤
17 መልካም ማድረግን ተማሩ፤ፍትሕን እሹ፣የተገፉትን አጽናኑ፤አባት ለሌላቸው ቁሙላቸው፤ለመበለቶችም ተሟገቱ።
18 “ኑና እንዋቀስ”ይላል እግዚአብሔር፤“ኀጢአታችሁ እንደ ዐለላ ቢቀላእንደ በረዶ ይነጣል፤እንደ ደም ቢቀላምእንደ ባዘቶ ነጭ ይሆናል።