18 “ኑና እንዋቀስ”ይላል እግዚአብሔር፤“ኀጢአታችሁ እንደ ዐለላ ቢቀላእንደ በረዶ ይነጣል፤እንደ ደም ቢቀላምእንደ ባዘቶ ነጭ ይሆናል።
19 እሺ ብትሉ፣ ብትታዘዙምየምድርን በረከት ትበላላችሁ፤
20 እምቢ ብላችሁ ብታምፁ ግንሰይፍ ይበላችኋል።” የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና።
21 ታማኝ የነበረችው ከተማእንዴት አመንዝራ እንደሆነች ተመልከቱቀድሞ ፍትሕ የሞላባት፣ጽድቅ የሰፈነባት ነበረች፤አሁን ግን የነፍሰ ገዳዮች ማደሪያ ሆነ
22 ብርሽ ዝጎአል፣ምርጥ የወይን ጠጅሽ ውሃ ገባው፤
23 ገዥዎችሽ ዐመፀኞችናየሌባ ግብረ ዐበሮች ናቸው፤ሁሉም ጒቦን ይወዳሉ፤እጅ መንሻንም በብርቱ ይፈልጋሉ፤አባት ለሌላቸው አይቆሙም፤የመበለቶችንም አቤቱታ አይሰሙም።
24 ስለዚህ ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣የእስራኤል ኀያል እንዲህ ይላል፤“በባላንጣዎቼ ላይ ቍጣዬን እገልጣለሁ፤ጠላቶቼንም እበቀላለሁ።