1 ፍትሕ የጐደለውን ሕግ ለሚያወጡ፣ጭቈና የሞላበትን ሥርዐት ለሚደነግጉ ወዮላቸው!
2 የድኾችን መብት ለሚገፉ፣የተጨቈነውን ሕዝቤን ፍትሕ ለሚያዛቡ፣መበለቶችን ለሚበዘብዙ፣ወላጅ የሌላቸውን ልጆች ለሚመዘብሩ ወዮላቸው!
3 በምትጐበኙበት ቀን ምን ይውጣችኋል?ጥፋት ከሩቅ ሲመጣስ ምን ትሆናላችሁ?ርዳታን ለማግኘትስ ወደ ማን ትሸሻላችሁ?ሀብታችሁንስ የት ታገኙታላችሁ?
4 ከእስረኞች ጋር ከመርበትበት፣ከታረዱትም ጋር ከመጣል በቀር ምንም አይተርፋችሁም።ይህም ሁሉ ሆኖ፣ ቍጣው ገና አልበረደም።እጁም እንደ ተዘረጋ ነው።
5 “የቍጣዬ በትር ለሆነ፣የመቅሠፍቴም ዱላ በእጁ ላለው ለአሦራዊው ወዮለት!
6 ሀብታቸውን እንዲዘርፍ፣ ምርኮን እንዲያግበሰብስ፣እንደ መንገድ ላይ ጭቃም እንዲረግጣቸው፣አምላክ በሌለው ሕዝብ ላይ እልከዋለሁ፣በሚያስቈጣኝም ሕዝብ ላይ እሰደዋለሁ።