5 “የቍጣዬ በትር ለሆነ፣የመቅሠፍቴም ዱላ በእጁ ላለው ለአሦራዊው ወዮለት!
6 ሀብታቸውን እንዲዘርፍ፣ ምርኮን እንዲያግበሰብስ፣እንደ መንገድ ላይ ጭቃም እንዲረግጣቸው፣አምላክ በሌለው ሕዝብ ላይ እልከዋለሁ፣በሚያስቈጣኝም ሕዝብ ላይ እሰደዋለሁ።
7 እርሱ ግን እንዲህ አላሰበም፤በልቡም ይህ አልነበረም፤ነገር ግን ዕቅዱ ለማጥፋት፣ብዙ ሕዝቦችንም ለመደምሰስ ነበር።
8 እንዲህም ይል ነበር፤‘የጦር አዛዦቼ በሙሉ ነገሥታት አይደሉምን?
9 ካልኖ እንደ ከርከሚሽ፣ሐማት እንደ አርፋድ፣ሰማርያስ እንደ ደማስቆ አይደሉምን?
10 የጣዖታትን መንግሥታት፣ምስሎቻቸው ከኢየሩሳሌምና ከሰማርያ መንግሥታት የሚበልጡትን እጄ እንደ ያዘች ሁሉ፣
11 በሰማርያና በጣዖቶቿ ያደረግሁትን፣በኢየሩሳሌምና በተቀረጹ ምስሎቿስ እንዲሁ አላደርግምን?።”