22 “በእነርሱ ላይ እነሣለሁ”ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።“ስሟንና ትሩፋኖቿን፣ዘሯንና ትውልዷን ከባቢሎን እቈርጣለሁ”ይላል እግዚአብሔር።
23 “የጃርት መኖሪያ፣ረግረጋማ ቦታ አደርጋታለሁ፤በጥፋትም መጥረጊያ እጠርጋታለሁ”ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
24 የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ምሎአል፤“እንደ ዐቀድሁት በርግጥ ይከናወናል፤እንደ አሰብሁትም ይሆናል።
25 አሦርን በምድሬ ላይ አደቃለሁ፤በተራራዬም ላይ እረግጠዋለሁ፤ቀንበሩ ከሕዝቤ ላይ ይነሣል፤ሸክሙም ከትከሻቸው ላይ ይወርዳል።”
26 ለምድር ሁሉ የታሰበው ዕቅድ ይህ ነው፤በአሕዛብም ሁሉ ላይ የተዘረጋው እጅ ይኸው ነው።
27 የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አስቦአል፤ማንስ ያግደዋል?እጁም ተዘርግቶአል?ማንስ ይመልሰዋል?
28 ንጉሡ አካዝ በሞተበት ዓመት እንዲህ የሚል ንግር መጣ፤