1 ስለ ደማስቆ የተነገረ ንግር፤“እነሆ፤ ደማስቆ ከእንግዲህ ከተማነቷ ይቀራል፤የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች።
2 የአሮኤር ከተሞች ባድማ ይሆናሉ፤የመንጎች መሰማሪያ ይሆናሉ፤የሚያስፈራቸውም የለም።
3 የተመሸገ ከተማ ከኤፍሬም፣የመንግሥት ሥልጣን ከደማስቆ ይወርዳል፤የሶርያም ቅሬታእንደ እስራኤላውያን ክብር ይሆናል”ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
4 “በዚያን ቀን የያዕቆብ ክብር ይደበዝዛል፤የሰውነቱም ውፍረት ይሟሽሻል።