2 የአሮኤር ከተሞች ባድማ ይሆናሉ፤የመንጎች መሰማሪያ ይሆናሉ፤የሚያስፈራቸውም የለም።
3 የተመሸገ ከተማ ከኤፍሬም፣የመንግሥት ሥልጣን ከደማስቆ ይወርዳል፤የሶርያም ቅሬታእንደ እስራኤላውያን ክብር ይሆናል”ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
4 “በዚያን ቀን የያዕቆብ ክብር ይደበዝዛል፤የሰውነቱም ውፍረት ይሟሽሻል።
5 አጫጅ የቆመውን ሰብል ሰብስቦ፣ዛላውንም በክንዱ እንደሚያጭድ፣ይህም በራፋይም ሸለቆእንደሚለቀም ቃርሚያ ይሆናል።
6 ሆኖም የወይራ ዛፍ ሲመታ፣ሁለት ወይም ሦስት ፍሬ በቅርንጫፍ ራስ ላይ እንደሚቀር፣አራት ወይም አምስት ፍሬም ችፍግ ባለው ቅርንጫፍ ላይ እንደሚቀር፣እንዲሁ ጥቂት ቃርሚያ ይተርፋል”ይላል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር።
7 በዚያ ቀን ሰዎች ወደ ፈጣሪያቸው ይመለከታሉ፤ዐይኖቻቸውም ወደ እስራኤል ቅዱስ ያያሉ።
8 በእጃቸውም ወደ ሠሯቸው መሠዊያዎች አይመለከቱም፤በጣቶቻቸው ላበጇቸው የዕጣን መሠዊያዎች፣ለአሼራም የአምልኮ ዐምዶችክብር አይሰጡም።