4 እግዚአብሔር እንዲህ ብሎኛል፤“ጸጥ ብዬ እቀመጣለሁ፤ከማደሪያዬም በፀሓይ ሐሩር እንደሚያ ብረቀርቅ ትኵሳት፣በመከርም ሙቀት እንደ ደመና ጠል ሆኜ እመለከታለሁ።”
5 ከመከር በፊት የአበባው ወቅት ሲያልፍ፣አበባው የጐመራ የወይን ፍሬ ሲሆን፣የወይን ሐረጉን ተቀጥላ በመግረዣ ይገርዘዋል፤የተንሰራፋውንም ቅርንጫፍ ቈራርጦ ያስወግደዋልና።
6 ሁሉም በተራራ ላይ ለሚኖሩ ነጣቂ አሞሮችለዱርም አራዊት ይተዋሉ፤አሞሮች በጋውን ሁሉ ሲበሉት ይባጃሉ፤የዱር አራዊትም ክረምቱን ሁሉ ሲበሉት ይከርማሉ።
7 በዚያን ጊዜ ለሰራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር፣ረጃጅምና ቈዳው ከለሰለሰ፣ከቅርብም ከሩቅም ከሚፈራ ሕዝብ፣ኀያልና ቋንቋው ከማይገባ፣ወንዞችም ምድሩን ከሚከፍሉት መንግሥት፣ገጸ በረከት ይመጣለታል፤ ገጸ በረከቱም የሚመጣለት የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ስም ወዳለበት ወደ ጽዮን ተራራ ነው።