1 በባሕሩ ዳር ባለው ምድረ በዳ ላይ የተነገረ ንግር፤ዐውሎ ነፋስ ከደቡብ እየጠራረገ እንደሚመጣ፣ወራሪ ከአሸባሪ ምድር፣ከምድረ በዳ ይመጣል።
2 የሚያስጨንቅ ራእይ አየሁ፤ከሓዲ አሳልፎ ይሰጣል፤ ዘራፊ ይዘርፋል።ኤላም ሆይ፤ ተነሺ ሜዶን ሆይ፤ ክበቢእርሷ ያደረሰችውን ሥቃይ ሁሉ አስቀራለሁ።
3 ወገቤ በዚህ ሥቃይ ተሞላ፤በምጥ ላይ እንዳለች ሴት ጭንቅ ያዘኝ፤በሰማሁት ነገር ተንገዳገድሁ፤ባየሁትም ነገር ተሸበርሁ።
4 ልቤ ተናወጠ፤ፍርሀት አንቀጠቀጠኝ፤የጓጓሁለት ውጋጋን፣ታላቅ ፍርሀት አሳደረብኝ።