11 ስለ ኤዶም የተነገረ ንግር፤አንዱ ከሴይር ጠርቶኝ፣“ጠባቂ ሆይ፤ ሊነጋ ምን ያህል ቀረው?ጠባቂ ሆይ፤ ሊነጋ ምን ያህል ቀረው?” አለኝ።
12 ጠባቂውም መለሰ፤“ይነጋል፤ ግን ተመልሶ ይመሻል፤መጠየቅ ከፈለጋችሁ፣ ጠይቁ፤ነገር ግን ተመልሳችሁ ኑ” አለ።
13 ስለ ዐረብ አገር የተነገረ ንግር፤እናንተ በዐረብ ዱር የምትሰፍሩ፣የድዳን ሲራራ ነጋዴዎች፣
14 ለተጠሙ ውሃ አምጡ።በቴማን የምትኖሩ፣ለስደተኞች ምግብ አምጡ።
15 ከሰይፍ፣ከተመዘዘ ሰይፍ፣ከተደገነ ቀስት፣ከተፋፋመ ጦርነት ሸሽተዋልና።
16 ጌታም እንዲህ አለኝ፤ ኋበውል የተቀጠረ ሠራተኛ ቀን እንደሚቈጥር፣ የቄዳር ክብር በአንድ ዓመት ውስጥ ያበቃለታል።
17 የተረፈው ቀስተኛ፣ የቄዳር ጦረኛ ጥቂት ይሆናል፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ተናግሮአልና።”