3 ወገቤ በዚህ ሥቃይ ተሞላ፤በምጥ ላይ እንዳለች ሴት ጭንቅ ያዘኝ፤በሰማሁት ነገር ተንገዳገድሁ፤ባየሁትም ነገር ተሸበርሁ።
4 ልቤ ተናወጠ፤ፍርሀት አንቀጠቀጠኝ፤የጓጓሁለት ውጋጋን፣ታላቅ ፍርሀት አሳደረብኝ።
5 ማእዱን አሰናዱ፤ምንጣፉን አነጠፉ፤በሉ፤ ጠጡ!እናንት ሹማምት ተነሡ፤ጋሻውን በዘይት ወልውሉ!
6 ጌታ እንዲህ አለኝ፤“ሂድ፤ ጠባቂ አቁም፤ያየውንም ይናገር፤
7 በፈረሶች የሚሳብ፣ሠረገሎችን ሲያይ፣በአህያ ላይ የሚቀመጡትን፣በግመል የሚጋልቡትን ሲመለከት፣ያስተውል፣በጥንቃቄም ያስተውል።”
8 ጠባቂው ጮኸ፤ እንዲህም አለ፤“ጌታ ሆይ፤ በየቀኑ ማማ ላይ ቆሜአለሁ፤በየሌሊቱም በቦታዬ አለሁ።
9 እነሆ፤ አንድ ሰው በፈረሶች በሚሳብበሠረገላ መጥቶአል፤እንዲህም ሲል መለሰ፣‘ባቢሎን ወደቀች፣ ወደቀየአማልክቷም ምስሎች ሁሉ፣ተሰባብረው ምድር ላይ ወደቁ።’ ”