5 ማእዱን አሰናዱ፤ምንጣፉን አነጠፉ፤በሉ፤ ጠጡ!እናንት ሹማምት ተነሡ፤ጋሻውን በዘይት ወልውሉ!
6 ጌታ እንዲህ አለኝ፤“ሂድ፤ ጠባቂ አቁም፤ያየውንም ይናገር፤
7 በፈረሶች የሚሳብ፣ሠረገሎችን ሲያይ፣በአህያ ላይ የሚቀመጡትን፣በግመል የሚጋልቡትን ሲመለከት፣ያስተውል፣በጥንቃቄም ያስተውል።”
8 ጠባቂው ጮኸ፤ እንዲህም አለ፤“ጌታ ሆይ፤ በየቀኑ ማማ ላይ ቆሜአለሁ፤በየሌሊቱም በቦታዬ አለሁ።
9 እነሆ፤ አንድ ሰው በፈረሶች በሚሳብበሠረገላ መጥቶአል፤እንዲህም ሲል መለሰ፣‘ባቢሎን ወደቀች፣ ወደቀየአማልክቷም ምስሎች ሁሉ፣ተሰባብረው ምድር ላይ ወደቁ።’ ”
10 በዐውድማ ላይ የተወቃህ ሕዝቤ ሆይ፤ከሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ከእስራኤል አምላክ፣የሰማሁትን እነግርሃለሁ።
11 ስለ ኤዶም የተነገረ ንግር፤አንዱ ከሴይር ጠርቶኝ፣“ጠባቂ ሆይ፤ ሊነጋ ምን ያህል ቀረው?ጠባቂ ሆይ፤ ሊነጋ ምን ያህል ቀረው?” አለኝ።