17 አንተ ኀያል ሰው ሆይ፤ ተጠንቀቅ፤ እግዚአብሔር አጥብቆ ሊይዝህ፣ በእጆቹም ጨብጦ ሊወረውርህ ነው።
18 አዙሮ አዙሮ እንደ ሩር አጡዞ፣ወደ ሰፊ አገር ይወነጭፍሃል፤አንተ የጌታህ ቤት ዕፍረበዚያ ትሞታለህ፤የክብር ሠረገሎችህም እዚያ ይቀራሉ።
19 ከማዕረግህ አወርድሃለሁ፤ከኀላፊነትህም ትባረራለህ።
20 “በዚያን ቀን አገልጋዬን፣ የኬልቅያስን ልጅ ኤልያቄምን እጠራለሁ፤
21 መጐናጸፊያህን አለብሰዋለሁ፤ መታጠቂያህን አስታጥቀዋለሁ፤ ሥልጣንህንም አስረክበዋለሁ። እርሱም በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ፣ ለይሁዳም ቤት አባት ይሆናል።
22 የዳዊትን ቤት መክፈቻ በጫንቃው ላይ አደርጋለሁ፤ እርሱ የሚከፍተውን ማንም አይዘጋም፤ የሚዘጋውንም ማንም አይከፍትም።
23 በአስተማማኝ ስፍራ እንደ ካስማ እተክለዋለሁ፤ ለአባቱም ቤት የክብር ዙፋን ይሆናል።