4 ስለዚህ፣ “ከእኔ ራቁ፤አምርሬ ላልቅስበት፣ስለ ሕዝቤ ጥፋት፣ልታጽናኑኝ አትሞክሩ” አልሁ።
5 እግዚአብሔር የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርበራእይ ሸለቆ፣የመጯጯኺያ የመረገጥና የሽብር፣ቅጥሮችን የማፈራረስ፣ወደ ተራሮችም የሚጮኽበት ቀን አለው።
6 ኤላም የፍላጻ ሰገባ፣ፈረሷንና ሠረገላዋን አዘጋጀች፤ቂርም ጋሻዋን አነገበች
7 መልካሞቹ ሸለቆዎችሽ በሠረገሎች ተሞልተዋል፤ፈረሰኞችም በከተማዪቱ በሮች ላይ ቆመዋል፤
8 የይሁዳን መከላከያዎች ገልጧል።በዚያን ቀን በዱር ግምጃ ቤት የነበረውን፣የጦር መሣሪያ ተመለከትህ፤
9 የዳዊት ከተማ፣ብዙ ፍርስራሾች እንዳሉበት አያችሁ፤በታችኛውም ኵሬ፣ውሃ አጠራቀማችሁ።
10 በኢየሩሳሌም ያሉትን ቤቶች ቈጠራችሁ፤ቅጥሩን ለመጠገንም ቤቶቹን አፈረሳችሁ።