9 የዳዊት ከተማ፣ብዙ ፍርስራሾች እንዳሉበት አያችሁ፤በታችኛውም ኵሬ፣ውሃ አጠራቀማችሁ።
10 በኢየሩሳሌም ያሉትን ቤቶች ቈጠራችሁ፤ቅጥሩን ለመጠገንም ቤቶቹን አፈረሳችሁ።
11 ለጥንቱ ኵሬ ውሃ የሚሆን፣በሁለቱ ቅጥሮች መካከል ውሃ ማጠራቀሚያ ሠራችሁ፤ነገር ግን ይህን ያደረገውን አልተመለከ ታችሁም፤ቀድሞ ዐቅዶ የሠራውንም አላስታወሳችሁም።
12 በዚያን ቀን ጌታ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣እንድታለቅሱና በዋይታ እንድትጮኹ፣ጠጒራችሁን እንድትነጩማቅም እንድትለብሱ ጠራችሁ።
13 ነገር ግን እነሆ፤ ተድላና ደስታ፣ፍሪዳ መጣልና ሙክት ማረድ፣ሥጋ መብላትና የወይን ጠጅ መጠጣት አለ፤“እንብላ እንጠጣነገ እንሞታለንና” አላችሁ።
14 የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይህን ገለጠልኝ፤ እንዲህም ሲል በጆሮዬ ሰማሁ፤ “ይህ ኀጢአት እስከምትሞቱበት ቀን ድረስ አይሰረይላችሁም” ይላል ጌታ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
15 ጌታ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ሂድና ይህን መጋቢ፣የቤቱንም ኀላፊ ሳምናስን እንዲህ በለው፤