1 እነሆ፤ እግዚአብሔር ምድርን ባድማ ያደርጋታል፤ፈጽሞ ያጠፋታል፤የፍርስራሽ ክምር ያደርጋታል፤ነዋሪዎቿንም ይበትናል።
2 ነገሩ ሁሉም አንድ ዐይነት ይሆናል፤በሕዝቡ ላይ የሚሆነው በካህኑ፣በአገልጋዩ ላይ የሚሆነው በጌታው፣በአገልጋይዋ ላይ የሚሆነው በእመቤቷ፣በገዢው ላይ የሚሆነው በሻጩ፣በተበዳሪው ላይ የሚሆነው በአበዳሪው፣በብድር ከፋይ ላይ የሚሆነው በብድር ሰጪው ይሆናል።
3 ምድር ፈጽሞ ባድማ ትሆናለች፤ጨርሶም ትበዘበዛለች፤ እግዚአብሔር ይህን ቃል ተናግሮአልና።
4 ምድር ትደርቃለች፤ ትረግፋለች፤ዓለም ትዝላለች፤ ትረግፋለች፤የምድርም መሳፍንት ይዝላሉ።
5 ምድር በሕዝቧ ትረክሳለች፤ሕግን ጥሰዋል፤ሥርዐትን ተላልፈዋል፤ዘላለማዊውንም ኪዳን አፍርሰዋል።