7 አዲሱ የወይን ጠጅ አለቀ፤ የወይኑም ተክል ደረቀ፤ደስተኞችም ሁሉ አቃሰቱ።
8 የከበሮ ደስታ ጸጥ አለ፤የጨፋሪዎች ጩኸት አበቃ፤ደስ የሚያሰኘውም በገና እረጭ አለ።
9 ከእንግዲህ እየዘፈኑ የወይን ጠጅ አይጠጡም፤መጠጡም ለሚጠጡት ይመራል።
10 የፈራረሰችው ከተማ ባድማ ሆነች፤የየቤቱም መግቢያ ተዘጋ።
11 በየአደባባዩ የወይን ጠጅ ያለህ እያሉ ይጮኻሉ፤ደስታው ሁሉ ወደ ሐዘን ይለወጣል፤ሐሤቱም ሁሉ ከምድር ገጽ ጠፍቶአል።
12 ከተማዪቱ ፈጽማ ፈርሳለች፤በሮቿም ደቀው ወድቀዋል።
13 የወይራ ዛፍ ሲመታ፣የወይንም ዘለላ ሲቈረጥ ቃርሚያ እንደሚቀር ሁሉ፣በምድሪቱ ላይ፣በሕዝቦችም ላይ እንዲሁ ይሆናል።