3 በአንተ ላይ ታምናለችና፣በአንተ የምትደገፈውን ነፍስፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ።
4 በእግዚአብሔር ለዘላለም ታመኑ፤ጌታ እግዚአብሔር የዘላለም ዐምባ ነውና።
5 በከፍታ የሚኖሩትን ዝቅ ዝቅ ያደርጋል፤ከፍ ከፍ ያለችውን ከተማ ያዋርዳል፤ወደ ምድር ይጥላታል፤ከትቢያም ጋር ይደባልቃታል።
6 እግር፣የተጨቋኞች እግር፣የድኾች ኮቴ ይረግጣታል።
7 የጻድቃን መንገድ ቅን ናት፤አንተ ቅን የሆንህ ሆይ፤የጻድቃንን መንገድ ታቃናለህ።
8 እግዚአብሔር ሆይ፤ በሕግህ ጐዳና በመሄድ፣አንተን ተስፋ አድርገናል፤ስምህና ዝናህ፣የልባችን ምኞት ነው።
9 ነፍሴ በሌሊት ትናፍቅሃለች፤መንፈሴም በውስጤ ትፈልግሃለች።ፍርድህ ወደ ምድር በመጣ ጊዜ፣የዓለም ሕዝቦች ጽድቅን ይማራሉ።