24 ገበሬ ሊዘራ መሬቱን ሲያዘጋጅ ያለ ማቋረጥ ያርሳልን?ጓሉን ሲከሰክስ፣ ዐፈሩን ሲያለሰልስ ይከርማልን?
25 ዕርሻውን አስተካክሎ፣ጥቍር አዝሙድና ከሙን አይዘራምን?ስንዴውንስ በትልሙ፣ገብሱን በተገቢ ቦታው፣አጃውንም በተመደበው ስፍራ አይዘራምን?
26 አምላኩ ያስተምረዋል፤ትክክለኛውንም መንገድ ያሳየዋል።
27 ጥቍር አዝሙድ በመውቂያ መሣሪያ አይወቃም፤ከሙን የሠረገላ መንኰራኵር አይሄድበትም፤ጥቍር አዝሙድ በበትር፣ከሙንም በዘንግ ይወቃል።
28 እንጀራን ለመጋገር እህል ይፈጫል፤ስለዚህ አንድ ሰው ለዘላለም እህል ሲወቃ አይኖርም።የመውቂያውን መንኰራኵር ቢያኼድበትም፣ፈረሶቹ አይደፈጥጡትም።
29 ይህ ሁሉ የሚሆነው በምክሩ ድንቅ በጥበቡታላቅ ከሆነው፣ከሰራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።