1 እነሆ፤ ጌታ፣የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርከኢየሩሳሌምና ከይሁዳድጋፉንና ርዳታውን፣የምግብና የውሃ ርዳታውን ሁሉ ይነሣል፤
2 ጀግናውንና ተዋጊውን፣ፈራጁንና ነቢዩን፣አስማተኛውንና ሽማግሌውን፣
3 የአምሳ አለቃውንና ባለ ማዕረጉን፣አማካሪውንና ጠቢቡን የእጅ ባለ ሙያ፣ብልኁንም ምትሀተኛ ይነሣል።
4 ልጆችን መሪዎቻቸው አደርጋለሁ፤ያልበሰሉ ሕፃናትም ይገዟቸዋል።