2 ጀግናውንና ተዋጊውን፣ፈራጁንና ነቢዩን፣አስማተኛውንና ሽማግሌውን፣
3 የአምሳ አለቃውንና ባለ ማዕረጉን፣አማካሪውንና ጠቢቡን የእጅ ባለ ሙያ፣ብልኁንም ምትሀተኛ ይነሣል።
4 ልጆችን መሪዎቻቸው አደርጋለሁ፤ያልበሰሉ ሕፃናትም ይገዟቸዋል።
5 ሕዝብ እርስ በርሱ ይጨቋቈናል፤ሰው በሰው ላይ፤ ባልንጀራ በባልንጀራው ላይ፣ወጣቱ በሽማግሌው ላይ፣ተራው ሰው በተከበረው ላይ ይነሣል።
6 ሰውም በአባቱ ቤትከወንድሞቹ አንዱን ይዞ፣“አንተ ልብስ ስላለህ መሪ ሁነን፤ይህንንም የፍርስራሽ ክምር ግዛ” ይለዋል።
7 እርሱ ግን በዚያ ቀን ድምፁን ከፍ አድርጎ፣“እኔ መፍትሔ አልሆንም፤በቤቴም ልብስና ምግብ የለኝም፤የሕዝብ መሪ አታድርጉኝ” ይላል።
8 ኢየሩሳሌም ተንገዳግዳለች፤ይሁዳም ለመውደቅ ተቃርባለች፤ንግግራቸውም ሆነ ድርጊታቸው እግዚአብሔርን የሚቃወም፣የክብሩንም መገኘት የሚያቃልል ነውና።