1 እናንት አሕዛብ ሆይ፤ ኑ አድምጡም፤እናንተ ሰዎች ሆይ፤ አስተውሉ።ምድርና በውስጧ ያለ ሁሉ፣ዓለምና ከእርሷ የሚበቅል ሁሉ ይስማ።
2 እግዚአብሔር አሕዛብን ሁሉ ተቈጥቶአል፤ቍጣውም በሰራዊታቸው ሁሉ ላይ ነው፤ፈጽሞ ያጠፋቸዋል፤ለዕርድም አሳልፎ ይሰጣቸዋል።
3 ከእነርሱም የተገደሉት ወደ ውጭ ይጣላሉ፤ሬሳቸው ይከረፋል፤ተራሮችም ደም በደም ይሆናሉ።
4 የሰማይ ከዋክብት ሁሉ ይሟሽሻሉ፤ሰማይ እንደ ብራና ይጠቀለላል፤የከዋክብት ሰራዊት ሁሉ፣ጠውልጎ እንደ ረገፈ የወይን ቅጠል፣ደርቆም እንደ ወደቀ የበለስ ቅጠል ይሆናሉ።
5 ሰይፌ በሰማያት እስኪበቃት ጠጥታለች፤እነሆ፤ ወደ ኤዶም፣ፈጽሞ ወዳጠፋሁት ሕዝብ ለፍርድ ወርዳለች።