4 የሰማይ ከዋክብት ሁሉ ይሟሽሻሉ፤ሰማይ እንደ ብራና ይጠቀለላል፤የከዋክብት ሰራዊት ሁሉ፣ጠውልጎ እንደ ረገፈ የወይን ቅጠል፣ደርቆም እንደ ወደቀ የበለስ ቅጠል ይሆናሉ።
5 ሰይፌ በሰማያት እስኪበቃት ጠጥታለች፤እነሆ፤ ወደ ኤዶም፣ፈጽሞ ወዳጠፋሁት ሕዝብ ለፍርድ ወርዳለች።
6 የእግዚአብሔር ሰይፍ በደም ተነክራለች፤ሥብ ጠግባለች፤በበግ ጠቦትና በፍየል ደም፣በአውራም በግ ኵላሊት ሥብ ተሸፍናለች። እግዚአብሔር በባሶራ ከተማ መሥዋዕት፣በኤዶምም ታላቅ ዕርድ አዘጋጅቶአልና።
7 ጐሽ አብሮአቸው፣ኮርማም ከወይፈን ጋር ይወድቃል፤ምድራቸው በደም ትርሳለች፤ዐፈራቸውም ሥብ በሥብ ይሆናል።
8 እግዚአብሔር የበቀል ቀን፣ስለ ጽዮንም የሚሟገትበት ዓመት አለውና።
9 የኤዶም ምንጮች ሬንጅ፣ዐፈሯ የሚቃጠል ድኝ፣ምድሯም የሚንበለበል ዝፍት ይሆናል።
10 እሳቷ ሌሊትና ቀን አይጠፋም፤ጢሷም ለዘላለም ይትጐለጐላል፤ከትውልድ እስከ ትውልድ ባድማ ትሆናለች፤ማንም በዚያ ዳግም አያልፍም።