16 ጌታ ሆይ፤ ሰዎች በእነዚህ ነገሮች ይኖራሉ፤መንፈሴም እንዲሁ በእነዚህ ሕይወትን ያገኛል፤ፈወስኸኝ፤በሕይወትም አኖርኸኝ።
17 እነሆ፤ በሥቃይ የተጨነቅሁት፣ለጥቅሜ ሆነ፤ከጥፋት ጒድጓድ፣በፍቅርህ ጠበቅኸኝ፤ኀጢአቴንም ሁሉ፣ወደ ኋላህ ጣልኽ።
18 ሲኦል አያመሰግንህም፤ሞት አያወድስህም፤ወደ ጒድጓድ የሚወርዱ፣የአንተን ታማኝነት ተስፋ አያደርጉም።
19 እኔ ዛሬ እንደማደርገው፣ሕያዋን እነርሱ ያመሰግኑሃል።ስለ አንተ ታማኝነትም፣አባቶች ለልጆቻቸው ይነግራሉ።
20 እግዚአብሔር ያድነኛል፤ስለዚህ በዕድሜ ዘመናችን ሁሉ፣ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ፣አውታር ባለው መሣሪያ እንዘምራለን።
21 ኢሳይያስም፣ “የበለስ ጥፍጥፍ ወስዳችሁ በዕባጩ ላይ አድርጉለት እርሱም ይፈወሳል” ብሎ ነበር።
22 ሕዝቅያስም፣ “ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እወጣ ዘንድ ምልክቱ ምንድን ነው?” ብሎ ነበር።