7 “ ‘እግዚአብሔር የገባልህን ቃል እንደሚፈጽምልህ፣ የእግዚአብሔር ምልክት ይህ ነው፤
8 በአካዝ የሰዓት መቍጠሪያ ደረጃ ላይ፣ የወረደውን የፀሓይ ጥላ በዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ እንዲመለስ አደርጋለሁ።’ ” ስለዚህ ወርዶ የነበረው የፀሓይ ጥላ ያንኑ ያህል ወደ ኋላ ተመለሰ።
9 የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ ከሕመሙ ከተፈወሰ በኋላ የጻፈው ጽሕፈት፤
10 እኔ፣ “በዕድሜዬ እኩሌታ፣በሲኦል ደጆች ማለፍ አለብኝን?የቀረውንስ ዘመኔን ልነጠቅ ይገባልን?” አልሁ።
11 እንዲህም አልሁ፤ “ዳግም እግዚአብሔርን፣ እግዚአብሔርን በሕያዋን ምድር አላይም፤ከእንግዲህም የሰውን ዘር አላይም፤በዚህ ዓለም ከሚኖሩትም ጋር አልሆንም።
12 ቤቴ እንደ እረኛ ድንኳን ተነቀለ፤ከእኔም ተወሰደ፤ሕይወቴን እንደ ሸማኔ ጠቀለልሁ፤ከመጠቅለያ ቈርጦኛል፤ከጠዋት እስከ ማታ ልትጨርሰኝ ፈጠንህ።
13 እስከ ማለዳ በትዕግሥት ጠበቅሁ፤እርሱ ግን እንደ አንበሳ ዐጥንቶቼን ሁሉ ሰባበረ፤ከጠዋት እስከ ማታም ልትጨርሰኝ ፈጠንህ።