1 “ደሴቶች ሆይ፤ በፊቴ ዝም በሉ፤አሕዛብ ኀይላቸውን ያድሱ፤ቀርበው ይናገሩ፤በፍርድም ፊት እንገናኝ።
2 “ከምሥራቅ አንዱን ያነሣው፣በጽድቅም ወደ አገልግሎቱ የጠራው ማን ነው?አሕዛብን አሳልፎ ሰጠው፤ነገሥታትን በፊቱ አስገዛለትበሰይፉም እንደ ትቢያ አቦነናቸው፤በቀስቱም በነፋስ እንደ ተበተነ ገለባ አደረጋቸው።
3 አሳደዳቸው ያለ ችግር ዐልፎ ሄደ፤እግሩም ቀድሞ ባልረገጠው መንገድ ተጓዘ።
4 ይህን የሠራና ያደረገ፣ትውልድን ከጥንት የጠራ ማን ነው?እኔ እግዚአብሔር ከፊተኛው፣ከኋለኛውም ጋር፤ እኔው ነኝ።”
5 ደሴቶች አይተው ፈሩ፤የምድር ዳርቾች ደነገጡ፤ቀረቡ፤ ወደ ፊትም መጡ።
6 እያንዳንዱ ይረዳዳል፤ወንድሙንም፣ “አይዞህ” ይለዋል።