10 እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤አምላክህ ነኝና አትደንግጥ።አበረታሃለሁ፤ እረዳሃለሁ፤በጽድቄም ቀኝ እጄ ደግፌ እይዝሃለሁ።
11 “እነሆ፤ የተቈጡህ ሁሉ፣እጅግ ያፍራሉ፤ ይዋረዳሉም፤የሚቋቋሙህ፣እንዳልነበሩ ይሆናሉ፤ ይጠፋሉም።
12 ጠላቶችህን ብትፈልጋቸው እንኳ፣አታገኛቸውም፤የሚዋጉህም፣እንዳልነበሩ ይሆናሉ።
13 እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ‘አትፍራ፤እረዳሃለሁ’ብዬ ቀኝ እጅህን እይዛለሁና።
14 አንት ትል ያዕቆብ፣ታናሽ እስራኤል ሆይ፤‘አትፍራ እኔ እረዳሃለሁ’ ” ይላል እግዚአብሔር፤የሚቤዥህ የእስራኤል ቅዱስ ነው።
15 “እነሆ፣ አዲስየተሳለና ብዙ ጥርስ ያለው ማሄጃ አደርግሃለሁ፤ተራሮችን ታሄዳለህ፤ ታደቃቸዋለህ፤ኰረብቶችንም ገለባ ታደርጋቸዋለህ።
16 ታበጥራቸዋለህ፤ ነፋስ ጠርጎ ይወስዳቸዋል፤ዐውሎ ነፋስም ይበትናቸዋል።አንተ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይልሃል፤በእስራኤል ቅዱስ ሞገስ ታገኛለህ።