3 አሳደዳቸው ያለ ችግር ዐልፎ ሄደ፤እግሩም ቀድሞ ባልረገጠው መንገድ ተጓዘ።
4 ይህን የሠራና ያደረገ፣ትውልድን ከጥንት የጠራ ማን ነው?እኔ እግዚአብሔር ከፊተኛው፣ከኋለኛውም ጋር፤ እኔው ነኝ።”
5 ደሴቶች አይተው ፈሩ፤የምድር ዳርቾች ደነገጡ፤ቀረቡ፤ ወደ ፊትም መጡ።
6 እያንዳንዱ ይረዳዳል፤ወንድሙንም፣ “አይዞህ” ይለዋል።
7 ባለጅ የወርቅ አንጥረኛውን ያበረታታዋል፤በመዶሻ የሚያሳሳውም፣በመስፍ ላይ የሚቀጠቅጠውን ያነቃቃዋል፤ስለ ብየዳም ሥራው፣ “መልካም ነው” ይለዋል፤የጣዖቱ ምስል እንዳይወድቅም በምስማር ያጣብቀዋል።
8 “አንተ ግን፣ ባሪያዬ እስራኤል፣የመረጥሁ ያዕቆብ፣የወዳጄ የአብርሃም ዘር ሆይ፤
9 ከምድር ዳርቻ ያመጣሁህ፣ከአጥናፍም የጠራሁህ፣‘አንተ ባሪያዬ ነህ’ ያልሁህ፤መረጥሁህ እንጂ፤ አልጣልሁህም።