18 “የቀደመውን ነገር አታስቡ፤ያለፈውን እርሱ።
19 እነሆ፤ አዲስ ነገር አደርጋለሁ፤እርሱም አሁን ይበቅላል፤ አታስተውሉትምን?በምድረ በዳም መንገድ አዘጋጃለሁ፤በበረሓም ምንጭ አፈልቃለሁ፤
20 የምድረ በዳ አራዊት፣ቀበሮና ጒጒት ያከብሩኛል፤በምድረ በዳ ውሃ፣በበረሓም ምንጭ እሰጣለሁና።ለመረጥሁት ሕዝቤ ውሃ እሰጣለሁ፤
21 ለራሴ ያበጀሁት ሕዝብምስጋናዬን ያውጅ ዘንድ ይህን አደርጋለሁ።
22 “ያዕቆብ ሆይ፤ አንተ ግን አልጠራኸኝም፤እስራኤል ሆይ፤ የእኔ ነገር ታክቶሃል።
23 ለሚቃጠል መሥዋዕት በጎች አላመጣህልኝም፤በመሥዋዕትህም አላከበርኸኝም።በእህል ቍርባን አላስቸገርሁህም፤በዕጣን መሥዋዕትም አላሰለቸሁህም።
24 መልካም መዐዛ ያለው ዕጣን አልገዛህልኝም፤በመሥዋዕትህ ሥብ አላጠገብኸኝም፤ነገር ግን የኀጢአት ሸክምህን ጫንህብኝ፤በበደልህም አደከምኸኝ።