23 ለሚቃጠል መሥዋዕት በጎች አላመጣህልኝም፤በመሥዋዕትህም አላከበርኸኝም።በእህል ቍርባን አላስቸገርሁህም፤በዕጣን መሥዋዕትም አላሰለቸሁህም።
24 መልካም መዐዛ ያለው ዕጣን አልገዛህልኝም፤በመሥዋዕትህ ሥብ አላጠገብኸኝም፤ነገር ግን የኀጢአት ሸክምህን ጫንህብኝ፤በበደልህም አደከምኸኝ።
25 “ስለ ራሴ ስል መተላለፍህን የምደመስ ስልህ፣እኔ፣ እኔው ነኝ፤ኀጢአትህን አላስባትም።
26 እስቲ ያለፈውን አስታውሰኝ፤ተቀራርበን እንከራከርበት፤ትክክለኛ ስለ መሆንህም አስረዳ።
27 የመጀመሪያው አባትህ ኀጢአት ሠርቶአል፤መምህሮችህም ዐምፀውብኛል።
28 ስለዚህ የመቅደስህን አለቆች አዋርዳለሁ፤ያዕቆብን ለጥፋት፣እስራኤልን ለስድብ እዳርጋለሁ።