ኢሳይያስ 43:8-14 NASV

8 ዐይን እያላቸው የታወሩትን፣ጆሮ እያላቸው የደነቈሩትን አውጣ።

9 ሕዝብ ሁሉ በአንድነት ይሰብሰብ፤ሰውም ይከማች፤ከእነርሱ አስቀድሞ ይህን የነገረን፣የቀድሞውን ነገር ያወጀልን ማን ነው?ሌሎችን ሰምተው፣ “እውነት ነው” እንዲሉ፣ትክክለኝነታቸውም እንዲረጋገጥ ምስክሮቻቸውን ያቅርቡ።

10 “ታውቁና ታምኑብኝ ዘንድ፣እርሱ እኔ እንደሆንሁ ትረዱ ዘንድ፣እናንተ ምስክሮቼ፣የመረጥሁትም ባሪያዬ ናችሁ” ይላል እግዚአብሔር።“ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም፤ከእኔም በኋላ አይኖርም።

11 እኔ፣ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ከእኔም ሌላ የሚያድን የለም።

12 ገልጫለሁ፤ አድኛለሁ፤ ተናግሬአለሁ፤በመካከላችሁ እኔ እንጂ ባዕድ አምላክ አልነበረም።እኔ አምላክ እንደሆንሁ፣ እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ” ይላል እግዚአብሔር፤

13 “ከጥንት ጀምሮ እኔው ነኝ፤ከእጄም ማውጣት የሚችል የለም፤እኔ የምሠራውን ማን ማገድ ይችላል?”

14 የእስራኤል ቅዱስ፣የሚቤዣችሁ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ስለ እናንተ በባቢሎን ላይ ሰራዊት እሰዳለሁ፤በሚመኩባቸውም መርከቦች፣ባቢሎናውያንን ሁሉ እንደ ኰብላይ አመጣለሁ።