1 ቤል ተዋረደ፤ ናባው እጅግ ዝቅ አለ፤ጣዖቶቻቸው በአጋሰስ ተጭነዋል፤ይዘዋቸው የሚዞሩት ምስሎች ሸክም ናቸው፤ለደከሙ እንስሳት ከባድ ጭነት ናቸው።
2 እነርሱም በአንድ ላይ ዝቅ ይላሉ፤ ያጐነብሳሉ፤ጭነቱን ለማዳን አይችሉም፤ራሳቸውም በምርኮ ይወሰዳሉ።
3 “እናንት የያዕቆብ ቤት ሆይ፤የእስራኤል ቤት ቅሬታ ሁሉ፣ከተፀነሳችሁበት ጊዜ ጀምሮ የያዝኋችሁ፣ከተወለዳችሁበት ጊዜ ጀምሮ የተሸከምኋችሁ ስሙኝ።
4 እስከ ሽምግልናችሁ፣ እስከ ሽበትም፣የምሸከማችሁ እኔ ነኝ፤ እኔው ነኝ።ሠርቻችኋለሁ፤ እሸከማችኋለሁ፤እደግፋችኋለሁ፤ አድናችኋለሁ።
5 “ከማን ጋር ታወዳድሩኛላችሁ? ከማንስ ጋር እኩል ታደርጉኛላችሁ?እንመሳሰልስ ዘንድ ከማን ጋር ታነጻጽሩኛላችሁ?