18 ኀጢአትን በማታለል ገመድ ለሚስቡ፣በደልንም በሠረገላ ማሰሪያ ለሚጐትቱ ወዮላቸው!
19 በዐይናችን እንድናይ እግዚአብሔር ይቸኵል፤ሥራውንም ያፋጥን፤የእስራኤልን ቅዱስ፣ የእርሱን ዕቅድእንድናውቃት ትቅረብ፤ትምጣም ለሚሉ ወዮላቸው!”
20 ክፉውን መልካም፣መልካሙን ክፉ ለሚሉብርሃኑን ጨለማ፣ጨለማውን ብርሃን ለሚያደርጉ፣ጣፋጩን መራራ፣መራራውንም ጣፋጭ ለሚያደርጉ ወዮላቸው!
21 ራሳቸውን እንደ ብልኅ ለሚቈጥሩ፣በራሳቸውም አመለካከት ጥበበኛ ለሆኑ ወዮላቸው!
22 የወይን ጠጅ ለመጠጣት ጀግኖች፣የሚያሰክር መጠጥ ለመደባለቅ ብርቱ ለሆኑ ወዮላቸው!
23 ጒቦን በመቀበል በደለኛን ንጹሕ ለሚያደርጉ፣ለበደል አልባ ሰው ፍትሕን ለሚነፍጉ ወዮላቸው!
24 ስለዚህ የእሳት ነበልባል ገለባን እንደሚበላ፣ድርቆሽም በእሳት ጋይቶ እንደሚጠፋ፣የእነርሱም ሥር እንዲሁ ይበሰብሳል፤አበባቸውም እንደ ትቢያ ይበናል፤የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ሕግ ንቀዋልና፤የእስራኤል ቅዱስ የተናገረውንም ቃል አቃለዋል።