ኢሳይያስ 5:5-11 NASV

5 እንግዲህ በወይኔ ቦታምን እንደማደርግ ልንገራችሁ፤ዐጥሩን እነቅላለሁ፤ለጥፋት ይጋለጣል፤ግንቡንም አፈርሳለሁ፣መረጋገጫም ይሆናል።

6 የማይኰተኰትና የማይታረምጠፍ መሬት አደርገዋለሁ፤ኵርንችትና እሾኽም ይበቅልበታል፤ዝናብም እንዳይዘንብበትደመናዎችን አዝዛለሁ።”

7 የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔርየወይን ቦታው የእስራኤል ቤት ነው፤የይሁዳ ሰዎችምየደስታው አትክልት ናቸው።ፍትሕን ፈለገ፤ ነገር ግን ደም ማፍሰስን አየ፤ጽድቅን ፈለገ፤ ነገር ግን የጭንቅን ጩኸት ሰማ።

8 ስፍራ ለሌሎች እስከማይተርፍ፣ቤትን በቤት ላይ በመጨመር፣መሬትን ከመሬት ጋር በማያያዝ፣ለብቻችሁ በምድር ተስፋፍታችሁ ለምትኖሩ ወዮላችሁ

9 የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ጆሮዬ እየሰማ እንዲህ ሲል ተናገረ፤“ታላላቅ ቤቶች ወና ይቀራሉ፣የሚያማምሩም ቤቶች ኗሪ ያጣሉ።

10 ከሩብ ጋሻ የወይን ቦታ አንድ የባዶስ መስፈሪያ ያህል የወይን ጭማቂ ብቻ ይገኛል፤ አንድ የቆሮስ መስፈሪያ ዘር ተዘርቶ አንድ የኢፍ መስፈሪያ እህል ብቻ ይሰጣል።

11 የሚያሰክር መጠጥ ፍለጋማልደው ለሚነሡ፣እስኪያነዳቸውም ወይን በመጠጣትሌሊቱን ለሚያነጉ ወዮላቸ