ኢሳይያስ 51:12-18 NASV

12 “የማጽናናችሁ እኔ፣ እኔው ብቻ ነኝ፤ሟች የሆኑትን ሰዎች፣እንደ ሣር የሚጠወልጉትን የሰው ልጆችለምን ትፈራለህ?

13 የፈጠረህን፣ሰማያትን የዘረጋውን፣ምድርን የመሠረተውን እግዚአብሔርን ረስተሃል፤ሊያጠፋህ ከተዘጋጀው፣ከጨቋኙ ቊጣ የተነሣ፣በየቀኑ በሽብር ትኖራለህ፤ታዲያ የጨቋኙ ቊጣ የት አለ?

14 ዐንገታቸውን የደፉ እስረኞች በፍጥነት ነጻ ይወጣሉ፤በታሰሩበትም ጒድጓድ ውስጥ አይሞቱም፤እንጀራ አያጡም።

15 ሞገዱ እንዲተም ባሕሩን የማናውጥ፣እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝና፤ስሙም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።

16 ቃሌን በአፍህ አኖርሁ፤በእጄ ጥላ ጋረድሁህ፤ሰማያትን በስፍራቸው ያስቀመጥሁ፣ምድርን የመሠረትሁ፣ጽዮንንም፣ ‘አንቺ ሕዝቤ ነሽ’ ያልሁ እኔ ነኝ።

17 ከእግዚአብሔር እጅ፣የቍጣውን ጽዋ የጠጣሽ፣ዝቃጩ እንኳ ሳይቀር፣ሰዎችን የሚያንገደግደውን ዋንጫ የጨለጥሽ፣ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ተነሺ፤ተነሺ፤ ተነሺ።

18 ከወለደቻቸው ወንዶች ልጆች ሁሉ፣የመራት አንድም አልነበረም፤ካሳደገቻቸው ወንዶች ልጆች ሁሉ፣እጇን ይዞ የወሰዳት ማንም አልነበረም።