ኢሳይያስ 56:1-7 NASV

1 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ፍትሕን ጠብቁ፤መልካሙን አድርጉ፤ማዳኔ በቅርብ ነው፤ጽድቄም ፈጥኖ ይገለጣልና።

2 ሰንበትን ሳያረክስ የሚያከብር፣ክፉን ከማድረግ እጁን የሚሰበስብ፣ የሚገታ፣እነዚህን የሚፈጽም ሰው የተባረከ ነው።”

3 ወደ እግዚአብሔር የተጠጋ መጻተኛ፣“እግዚአብሔር በርግጥ ከሕዝቡ ይለየኛል” አይበል፤ጃንደረባም፣“እኔ ደረቅ ዛፍ ነኝ” አይበል።

4 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ሰንበቶቼን ለሚያከብሩ ጃንደረቦች፣ደስ የሚያሰኘኝን ለሚመርጡ፣ቃል ኪዳኔን፣ ለሚጠብቁ

5 በቤተ መቅደሴና በቅጥሮቼ ውስጥ፣ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች የበለጠ፣መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ለዘላለም፣የማይጠፋ ስም እሰጣቸዋለሁ።

6 እርሱን ለማገልገል፣ራሳቸውን ከእግዚአብሔር ጋር ያቈራኙ መጻተኞች፣ የእግዚአብሔርን ስም በመውደድ፣እርሱንም በማምለክ፣ሰንበትን ሳያረክሱ የሚያከብሩትን ሁሉ፣ቃል ኪዳኔንም የሚጠብቁትን፣

7 ወደ ተቀደሰው ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፤በጸሎት ቤቴም ውስጥ ደስ አሰኛቸዋለሁ።የሚቃጠል መሥዋዕታቸውንና ሌሎች መሥዋዕቶቻቸውን፣በመሠዊያዬ ቢሠዉ እቀበላቸዋለሁ፤ቤቴ፣ ለሕዝቦች ሁሉየጸሎት ቤት ተብሎ ይጠራልና።”