1 ጻድቅ ይሞታል፤ይህን ግን ማንም ልብ አይልም፤ ለእግዚአብሔር ያደሩ ሰዎች ይወሰዳሉ፤ጻድቃን ከክፉ ይድኑ ዘንድ፣መወሰዳቸውን፣ማንም አያስተውልም።
2 በቅንነት የሚሄዱ፣ሰላም ይሆንላቸዋል፤መኝታቸው ላይ ያርፋሉ።
3 “እናንት የአስማተኛዪቱ ልጆች ግን፣እናንት የአመንዝራውና የጋለሞታዪቱ ዘር፤ እናንት፣ ወዲህ ኑ፤
4 የምትሣለቁት በማን ላይ ነው?የምታሽሟጥጡት ማንን ነው?ምላሳችሁንስ አውጥታችሁ የምታሾፉት በማን ላይ ነው?እናንት የዐመፀኞች ልጆች፣የሐሰተኞች ዘር አይደላችሁምን?