1 “በኀይል ጩኽ፤ ምንም አታስቀር፤ድምፅህን እንደ መለከት አሰማ፤ለሕዝቤ ዐመፃቸውን፣ለያዕቆብም ቤት ኀጢአታቸውን ተናገር።
2 ዕለት በዕለት ይፈልጉኛል፤መንገዴን ለማወቅ የሚጓጉ ይመስላሉ፤ትክክለኛውን ነገር እንደሚያደርግ፣የአምላኩንም ትእዛዝ እንዳልተወ ሕዝብ ሁሉ፣ተገቢ የሆነ ፍትሕ ይለምኑኛል፤እግዚአብሔር ወደ እነርሱ እንዲቀርብ የሚወዱም ይመስላሉ።
3 ‘አንተ ካልተቀበልኸው፣ስለ ምን ብለን ጾምን?አንተ ከጒዳይ ካልቈጠርኸው፣ስለ ምን ራሳችንን አዋረድን?’ ይላሉ።“ሆኖም በጾማችሁ ቀን የልባችሁን ታደርጋላችሁ፤ሠራተኞቻችሁንም ትበዘብዛላችሁ።
4 ጾማችሁ በጥልና በክርክር፣በግፍ ጡጫና በመደባደብ ይፈጸማል፤ከእንግዲህ ዛሬ እንደምትጾሙት ጾማችሁ፣ድምፃችሁ ወደ ላይ እንደሚሰማም ተስፋ አታድርጉ።