1 እነሆ፤ የእግዚአብሔር እጅ ከማዳን አላጠረችም፤ጆሮውም መስማት አልተሳናትም
2 ነገር ግን በደላችሁከአምላካችሁ ለይቶአችኋል፤ኀጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል፤በዚህም ምክንያት አይሰማም።
3 እጆቻችሁ በደም፣ጣቶቻችሁ በበደል ተነክረዋል፤ከንፈሮቻችሁ ሐሰትን ተናገሩ፤ምላሶቻችሁ ክፉ ነገርን አሰሙ።
4 ፍትሕን የሚጠራ ማንም የለም፤ጒዳዩን በቅንነት የሚያቀርብ የለም፤በከንቱ ነገር ታመኑ፤ ሐሰትን ተናገሩ፤ሁከትን ፀነሱ፤ ክፋትንም ወለዱ።