ኢሳይያስ 6:8-13 NASV

8 ከዚያም የጌታ ድምፅ፣ “ማንን እልካለሁ? ማንስ ይሄድልናል?” ሲል ሰማሁት።እኔም፣ “እነሆኝ፤ እኔን ላከኝ” አልሁ።

9 እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “ወደዚህ ሕዝብ ሂድ፤“ ‘መስማትን ትሰማላችሁ፤ ነገር ግን አታስተውሉም፤ማየትንም ታያላችሁ፤ ነገር ግን ልብ አትሉም’ ብለህ ንገራቸው።

10 የዚህን ሕዝብ ልብ አደንድን፤ጆሮአቸውን ድፈን፤ዐይኖቻቸውንም ክደን፤ይህ ካልሆነማ፣በዐይናቸው አይተው፣ በጆሮአቸው ሰምተው፣በልባቸውም አስተውለውበመመለስ ይፈወሳሉ።”

11 እኔም፣ “ጌታ ሆይ፤ ይህ የሚሆነው እስከ መቼ ነው?” አልሁት፤እርሱም መልሶ እንዲህ አለኝ፤“ከተሞች እስኪፈራርሱና፣የሚኖሩባቸው እስኪያጡ፣ቤቶችም ወና እስኪሆኑና፣ምድርም ፈጽሞ ባድማ እስክትሆን ድረስ፤

12 እግዚአብሔርም ሰዎችን እስከሚያርቅ፣ምድሪቱም ጨርሶ ባዶ እስክትሆን፣

13 ከዐሥር አንድ ሰው እንኳ በምድሪቱ ቢቀር፣እርሱም ደግሞ ይጠፋል፤ነገር ግን የኮምበልና የባሉጥ ዛፍ በተቈረጠጊዜ ጒቶ እንደሚቀር፣ቅዱሱም ዘር እንዲሁ በምድሪቱ ጒቶ ሆኖ ይቀራል።”