ኢሳይያስ 60:9-15 NASV

9 በርግጥ ደሴቶች እኔን ተስፋ ያደርጋሉ፤እርሱ ክብሩን ስላጐናጸፈሽ፣ለእስራኤል ቅዱስ፣ ለእግዚአብሔር አምላክሽ ክብር፣ከሩቅ ወንዶች ልጆችሽን፣ከነብራቸውና ከነወርቃቸው ለማምጣት፣የተርሴስ መርከቦች ቀድመው ይወጣሉ።

10 “ባዕዳን ቅጥሮችሽን ይሠራሉ፤ነገሥታቶቻቸው ያገለግሉሻል፤በቊጣዬ ብመታሽም፣ርኅራኄዬን በፍቅር አሳይሻለሁ።

11 በሮችሽ ምንጊዜም የተከፈቱ ይሆናሉ፤ቀንም ሆነ ሌሊት ከቶ አይዘጉም፤ይህም ሰዎች የመንግሥታትን ብልጥግና ወደ አንቺ እንዲያመጡ፤ነገሥታታቸውም በድል ወደ አንቺ እንዲገቡ ነው።

12 ለአንቺ የማይገዛ ሕዝብና መንግሥት ይጠፋል፤ፈጽሞም ይደመሰሳል።

13 የመቅደሴን ቦታ ለማስጌጥ፣የሊባኖስ ክብር፣ጥዱ፣ አስታውና ባርሰነቱ በአንድነት ወደ አንቺ ይመጣሉ፤እግሬ የሚያርፍበትንም ስፍራ አከብራለሁ።

14 የአስጨናቂዎችሽ ወንዶች ልጆች እየሰገዱ ወደ አንቺ ይመጣሉ፤የናቁሽም ሁሉ እግርሽ ላይ ይደፋሉ፤ የእግዚአብሔር ከተማ፣የእስራኤል ቅዱስ ገንዘብ የሆንሽው ጽዮን ብለው ይጠሩሻል።

15 “የተተውሽና የተጠላሽ፣ማንም ሰው የማያልፍብሽ ብትሆኝም እንኳ፣እኔ የዘላለም ትምክሕት፣የትውልድም ሁሉ ደስታ አደርግሻለሁ።