9 የኤፍሬም ራስ ሰማርያ፣የሰማርያም ራስ የሮሜልዩ ልጅ ነው።እንግዲህ በእምነታችሁ ካልጸናችሁ፣ፈጽሞ መቆም አትችሉም።’ ”
10 እንደ ገናም እግዚአብሔር አካዝን እንዲህ አለው፤
11 “ከጥልቁ ጥልቅ ወይም ከከፍታው ከፍታ ምልክት እንዲሰጥህ ከእግዚአብሔር ከአምላክህ ለምን።”
12 አካዝ ግን፣ “አልለምንም፣ እግዚአብሔርንም አልፈታተንም” አለ።
13 ኢሳይያስም እንዲህ አለ፤ “እናንተ የዳዊት ቤት ሆይ፤ ስሙ፤ የሰውን ትዕግሥት መፈታተናችሁ አንሶ የአምላኬን ትዕግሥት ትፈታተናላችሁን?
14 ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፤ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።
15 ክፉውን መተውና መልካሙን መምረጥ ሲችል ቅቤና ማር ይበላል።