1 ነገር ግን ተጨንቀው የነበሩ ከእንግዲህ ተስፋ ቢስ አይሆኑም። በቀደመው ዘመን የዛብሎንንና የንፍታሌምን ምድር አዋረደ፤ በሚመጣው ዘመን ግን ከዮርዳኖስ ማዶ፣ በባሕር መንገድ አጠገብ ያለውን የአሕዛብን ገሊላ ያከብራል፤
2 በጨለማ የሚኖር ሕዝብታላቅ ብርሃን አየ፤በሞት ጥላ ምድር ለኖሩትምብርሃን ወጣላቸው።
3 ሕዝብን አበዛህ፤ደስታቸውንም ጨመርህ፤ሰዎች ምርትን ሲሰበስቡ፣ምርኮንም ሲከፋፈሉደስ እንደሚላቸው ሁሉ፣እነርሱም በፊትህ ደስ ይላቸዋል።
4 ምድያም ድል በተመታ ጊዜ እንደሆነው፣የከበዳቸውን ቀንበር፣በትከሻቸው ላይ የነበረውን በትር፣የተጨቈኑበትንም ዘንግ ሰብረህላቸዋል።
5 የጦረኞች ጫማ ሁሉ፣በደም የተለወሰ ልብስም ሁሉ፣ለእሳት ይዳረጋል፤ይማገዳልም።
6 ሕፃን ተወልዶልናልና፤ወንድ ልጅ ተሰጥቶናል፤አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል።ስሙም፣ ድንቅ መካር፣ኀያል አምላክ፣የዘላለም አባት፣ የሰላም ልዑል ይባላል።
7 ለመንግሥቱ ስፋት፣ለሰላሙም ብዛት ፍጻሜ የለውም፤ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም፣መንግሥቱን በፍትሕና በጽድቅ ይመሠርታል፤ደግፎ በመያዝም ያጸናዋል።በዳዊት ዙፋን ይቀመጣል፤አገሩንም ሁሉ ይገዛል፤የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ቅናትይህን ያደርጋል።