ኢሳይያስ 9:12-18 NASV

12 ሶርያውያን ከምሥራቅ፣ ፍልስጥኤማውያን ከምዕራብ፤አፋቸውን ከፍተው እስራኤልን ይቦጫ ጭቋታል።ይህም ሁሉ ሆኖ፣ ቍጣው ገና አልበረደም፤እጁ እንደ ተዘረጋ ነው።

13 ሕዝቡ ግን ወደ ቀጣቸው ፊታቸውን አልመለሱም፤የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርንም አልፈለጉም።

14 ስለዚህ እግዚአብሔር ራስንና ጅራትን፣የዘንባባውን ቅርንጫፍና ሸምበቆውን ከእስራኤል በአንድ ቀን ይቈርጣል።

15 ሽማግሌዎችና የተከበሩ ሰዎች ራስ፣ሐሰትን የሚያስተምሩ ነቢያት ደግሞ ጅራት ናቸው።

16 ይህን ሕዝብ የሚመሩት ያስቱታል፤የሚመራውም ሕዝብ ከመንገድ ወጥቶ ይባዝናል።

17 ስለዚህ ጌታ በጐበዛዝት ደስ አይሰኝም፤አባት ለሌላቸውና ለመበለቶች አይራራም፤ ሁሉም ፈሪሀ እግዚአብሔር ያላደረ በትና ክፉ አድራጊ ነው፤የሁሉ አፍ አስጸያፊ ቃል ይናገራልና።ይህም ሁሉ ሆኖ፣ ቍጣው ገና አልበረደም፤እጁም እንደ ተዘረጋ ነው።

18 እንግዲህ ርኵሰት እንደ እሳት ይቀጣጠላል፤እሾህንና ኵርንችትን ይበላል፤ጥቅጥቅ ያለውን ደን ያነዳል፤ጢሱም ተትጐልጒሎ እንደ ዐምድ ይቆማል።