ኢሳይያስ 9:6-12 NASV

6 ሕፃን ተወልዶልናልና፤ወንድ ልጅ ተሰጥቶናል፤አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል።ስሙም፣ ድንቅ መካር፣ኀያል አምላክ፣የዘላለም አባት፣ የሰላም ልዑል ይባላል።

7 ለመንግሥቱ ስፋት፣ለሰላሙም ብዛት ፍጻሜ የለውም፤ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም፣መንግሥቱን በፍትሕና በጽድቅ ይመሠርታል፤ደግፎ በመያዝም ያጸናዋል።በዳዊት ዙፋን ይቀመጣል፤አገሩንም ሁሉ ይገዛል፤የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ቅናትይህን ያደርጋል።

8 ጌታ በያዕቆብ ላይ ቃል ላከ፤በእስራኤልም ላይ ይወድቃል።

9 ሕዝቡ በሙሉ፣ኤፍሬምና የሰማርያ ነዋሪዎችይህን ያውቃሉ፤በትዕቢትና በልብ እብሪትም እንዲህ ይላሉ፤

10 “ጡቦቹ ወድቀዋል፤እኛ ግን በጥርብ ድንጋይ መልሰን እንገነባለን፤የሾላ ዛፎቹ ተቈርጠዋል፤እኛ ግን በዝግባ እንተካለን።”

11 ነገር ግን እግዚአብሔር የረአሶንን ጠላቶች ያጠናክራል፤በእነርሱም ላይ ያመጣባቸዋል፤ባለጋራዎቻቸውንም ያነሣሣባቸዋል።

12 ሶርያውያን ከምሥራቅ፣ ፍልስጥኤማውያን ከምዕራብ፤አፋቸውን ከፍተው እስራኤልን ይቦጫ ጭቋታል።ይህም ሁሉ ሆኖ፣ ቍጣው ገና አልበረደም፤እጁ እንደ ተዘረጋ ነው።